Sunday School Choir

ወዳጄ ሆይ

ወዳጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ
የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ
የተዘጋች መቅደስ ንፂህት ኣዳራሽ

ሕዝቅኤል ያየሽ የምስራቅዋ በር
ማንም ያልገባባት ካአምላክ በስተቀር
የልኡል ማደርያ አማናዊት መቅደስ
ስለንፅህናሽ ምስጋናን እናቅርብ
ኣዝ

ሁለን ም የሆንሽ እናትና ድንግል
ማሂደረ መለኮት ወላዲተ ቃል
ያለዘርኣ ብእሲ ፉፁም ድንግልና
ኣምላክን የወለድሽ ሃመልማል ዘሲና
ኣዝ

ምስራቀ ምስራቃት ድንግል ሆይ ኣንቺ ነሽ
ጨረቃን የምትመስይ ፀሐይን የወለድሽ
የማለዳ ብርሃን ለዓይን የምታሳሺ
ፅዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ ኣትሸሺ
ኣዝ

Download it from Here

እኔስ በምግባሬ

እኔስ በምግባሬ ደካማ ሁኛለው (2)
እዘንልኝ ድንግል እለምንሻለው (2)
ያንን የእሳት ባህር እንዳላይ ኣደራ
እዘንልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ (2)
የዳዊት መሰንቆ የኤልያስ መና
የናሆም መድሃኒት ንኢ በደመና (2)
ኣዝ

ኣንቺ ነሽ ጉልበቴ በደከመኝ ግዜ
የልቤ መፅናኝ ረዳቴ ሙርኩዜ (2)
ኣዝ

ኣፈሳለሁ እምባ በጣም ተጨንቄ
እማፀንሻለው በደሌን ኣውቄ (2)
ኣዝ

Download it from here

ኣልፈርድም እኔ

ኣልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ሀጥያት
በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌታ ሲመጣ በሐይል በስልጣን

በቸርነቱ ኣምላክ ባይተወው በደሌም ሁሉ
ውሽጤ ቢፈተሽ በተሰጠኝ በቅዱስ ቃሉ
በምን ምግባሬ በሰው እፈርዳለሁ ኣይኔን ኣቅንቼ
በደሌ በዝቶ ለራሴ ሳላውቅ ለሐጥያቶቼ
ኣዝ

ይልቅ የኣንዱን ሸክም ሌላው ሰው ኣዝሎ ማጓዝ ይሻላል
መፍረድ ከመጣ ኣንድ ሰው ኣይልም ሁሉም በድለዋል
ወንድም ወንዱሙ እየከሰሰው በፍርድ ኣቁሞ
ኣህዛብ ያያል በንትርኩ እጅግ ተገርሞ
ኣዝ

ክርስትያን ሆኖ ከወንዱሙ ጋር እየተጣላ
ኣለም ዳኘቹው በሰው ፍርድቤት ታረቁ ብላ
ክርስትያን ሆኖ በኣህዛብ መሀል እየተካሰሰ
ኣምላክ ኣዘነ የመስቀሉ ስር ኣላማ ስተም
ኣዝ

መቸ ከሰሰ የከሰሱትን የገረፉትን
ኣይተናል እንጂ ለጠላቶቹ ምህረት ሲለምን
በፅድቅ ስራ ለእውነት ብለን መጥተናል እንጂ
ማነው የሾመው በወንድሞች ላይ ኣርጎ ፈራጂ
ኣዝ

Download it from here

ሀራሲ

ሀራሲ በእርፈ መስቀል ሰባኪ ወንጌል ኣባ ተክለሃይማኖት ክብር (2)
በእሲ እር በእሲ እግዚአብሔር ለአህዛበ መምህር
ትክበር ነብስየ በቅድሜክዮም (2)

Download it from here

ምንተኑ

ምንተኑ አአስየኪ እሴተ
በእንተ ኩሉ ዘገበርኪ ሊተ

የቅዱሳን ተስፋ የትንቢት ምዕራፍ
የስደተኞች ስንቅ የምህረት ደጃፍ

የፍጥረት መመኪያ ምክንያተ ድኂን
ለእኔም ለመንገዴ ስለሆንሽኝ ብርሃን
አዝ

የዓለም ኑሮ ማርኮኝ ልቤ ሲዋልል
በፈተናው ብዛት በህይወት ስዝል
ለሥጋዬ ፈቃድ ከቶ ስላልተውሽኝ
ለነፍሴም ሠላምን ስላስገኘሽልኝ
አዝ

በኃጢአት መጐስቆሌን ደካሜን ሳታይ
በኃዘን በችግሬ ከእኔ ሳትለይ
ከመከራዬ አዘቅት በአንቺ ስለወጣሁ
ለብዙ ውለታሽ ምን እከፍልሻለሁ
አዝ

Download it from here

ጌታ ሆይ ውለታህ

ጌታ ሆይ ውለታህ ታምርህ ድንቅነው
ኣምላካዊ ቃል ስምህ ሂይወቴ ነው (2)
ኣዝ

በሀዋርያት ኣድረህ ብዙ መክረህኛል
ስለሀጥያቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተህኛል
ኣዝ

በሀዘኔ ፈጥነህ ኣረጋጋሀኝ
ኣይዞህ ልጄ ብለህ ስወድቅ ያነሳሀኝ
ከማይጠፋው እሳት ከሞት ኣወጣሀኝ
ላንተ የምከፍልህ ምን ስጦታ ኣለኝ
ኣዝ

እውነተኛ እርዳታ ወገኔ ኣንተ ነህ
ጌታየ ከእናት ልጅ እጅግ ትበልጣለህ
መታመን ባንተ ነው ደግሞም መመካት
ወቅት የማይለውጥህ የማታውቅ ወረት

ስምህ ምግቤ ሆኖ ስጠራህ እጠግባለሁ
ፍቅርህን ቀምሼ ፍፁም እረካለሁ
በሰማይ በምድር ለነብፍም ለስጋ
ባንተ እመካለሁ ኣልፋ ና ኦሜጋ

Download it from here

እግዚኣብሔ ሆይ እርዳኝ

እግዚኣብሔ ሆይ እርዳኝ ቸርነት አድርገህ
እድሜ ለንስሐ እንደ ሕዝቅያስ ስጥተህ
ጠማማውን ልቤን በቃልህ ኣቅንተህ

ኣላውቀውም ብሎ ሲጠየቅ ያመጸው
ደሮ እስኪጮህ ድረስ ሦስት ግዜ የካደው
የጅረት ወንዝ ነው የሰጠኸው እንባ
ጴጥሮስ ተጸጽቶ ንስሐ እንዲገባ
አዝ

ጽዋው እንዳይደርሰኝ የኣይሁድ እድል
ልጅህ ሆኖ ውሎ ማታ መኮብለል
ጴጥሮስ እድለኛው ኣልቅሶ ተማረ
በትዕቢቱ ይሁዳ እንደወጣ ቀረ
እዝ

ዘመኗን በሙሉ በዝሙት ኣቃጥላ
በንስሐ ጠራት ጌታ በገሊላ
ታድሳ ተነሳች በእንባዋ ብዛት
እግሩ ስር ተደፍታ ማርያም መግደላዊት
አዝ

ኣመጸኛው ልቤ ዛሬስ መች ይተኛል
በሐጥያት በዝሙት በሥርቆት ይዋኛል
ወደ ቀድሞ ግብር እንዳይመለስ
ፍቅርህ በኔ ሰርጾ ኃጢአቴን ደምስስ
አዝ

በደላችን ሁሉ ሳታስብ ትተህ
በምጽኣት ሰዓት ከጻድቃን ቆጥረህ
ነጭ ልብስን ለብሰን ሆነን ካንተ ጋራ
በሩ ሳይዘጋ ኣስገባን ኣደራ
አዝ

Download it from here

አብርሃምን ከካራን የጠራኸው ጌታ

አብርሃምን ከካራን የጠራኸው ጌታ
ለሙሴ በሲና የሆንከው መከታ
ልንጠፋ ነውና በሥጋ ፍላጎት
የይስሐቅም ቤዛ ህይወቴን ታደጋት (2)

የኤርትራን ባህር በኃይልህ የከፈልክ
በሲና በረሃ ህዝብህን የመገብክ
ኖህ ከጥፋት ውሃ የዳነብህ አምላክ
ሎጥን እንዳዳንከው ፍጹም ምህረትህን ላክ (2)

የተነበዩልህ ነቢያት በሙሉ
አምላክ ሰው ይሆናል ይወለዳል ሲሉ
ከዓሣ አንበሪ ሆድ ዮናስን ያወጣህ
ዓለም ልትውጠኝ ነው አይለየኝ ፀጋህ (2)

ሥጋን ተዋህደህ በወሰንከው ስዓት
የሞትክልኝ አምላክ ያዳንከኝ ከሞት ሞት
እንደ ወንጌልህ ህግ የምኖር አድርገኝ
በመጨረሻው ቀን በቀኝህ እንድገኝ (2)

አልቻልኩኝምና ልፈጽም ህግህን
የሐዋርያት አጽናኝ ስጠኝ ብርታትህን
ምግባረ ጎደሎ ሆኛለሁኝና
የቅዱሳን አምላክ እርዳኝ እንድጸና (2)

Download it from here

ትሞታለህ እና

ትሞታለህ እና ቤትክን አስተካክል
ዝግጁ ሁን እንጂ ቋሚ ነኝ አትበል

ትናንት የነበሩ ዛሬ የሉም እና
ለተመኙት ሁሉ አልደረሱም እና
ለአሁንዋን ስዓት ለማየት አልበቁም
ተዘጋጅተ ጠብቅ ተረኛነህ አንተም
ኣዝ

ዛሬ እያለቀስህ የሞተውን ብትቀብር
አንተም እንደ እርሱ ትሆናለህ እና
ይልቅ ወንድሜ ሆይ ለራስህ አልቅስ
አፈር መሆንህም ሁልግዜ አስታውስ
ኣዝ

እሮጦ መቅደም ዘመንህ ያልፋል
ወድቀህ መነሳት ያን ግዜ ይደክማል
በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን ካሰብህ
በጠላት አትወድቅም ድል ታደርገዋለህ
ኣዝ

Download it from here

ዓለምን ዙሬ

ዓለምን ዙሬ አየሁት ሁሉም በተራ ቀመስኩት
ፈጽሞ የለም (2) ሰላም እንደልጅሽ ቤት

ሃብቴን ንብሬቴን ጨረስኩና ጉልበቴን ሁሉ ደከምና
ጎስቋላ ሁንኩኝ (2) ደካማ የሌለው ጤና

ስቃ አሳስቃ ተቀብላ መልኳን አውባ ተኳኩላ
ዘሬ ጣለችኝ (2) ይህች ዓለም አይረባም ብላ

የትናንትና ወዳጆቼ ዘሬ ሲሆኑ ጠላቶቼ
ባክኘ ቀረሁኝ (2) በዓለም ላይ ተንከራትቼ

የአባቴ ቤት ሲናፍቀኝ ፍቅሩን ምህረቱን ትዝ ሲለኝ
ሁሉንም ትቼ (2) ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ

ልጁም ዳልባል ባይገባኝ ባርያው
እሆን ዘንድ ቢፈቅድልኝ
ጎስቋላ ልጅህ ደካማው ልጅህ ድንግል ሆይ ዛሬ መጣሁኝ

እናቴን ኣንቺን ንቄ ትቼ የአባቴን ቤትን እረስቼ
ተሰቃየሁኝ ተንከራተትኩኝ ልደሰት በዓለም ገብቼ
አባቴን ስያየኝ ተደስቶ ጎረቤቶችን ሁሉን ጠርቶ
ሰርጉን ደገሰ (2) የበደልኩትን እረስቶ

እስካሁን ድረስ በድያለሁ ኣለም ደህናሁኝ አብቅቻለሁ
ወደ አባቴ ቤት (2) ዳግመኛ ተመልሻለሁ

Download it from here

ኦ ሚካኤል

ኦ ሚካኤል (2) ሊቀ መላእክት
በሐጥያት እንዳንወድቅ እንዳንሞት ፈጥነህ ተራዳን አጽናን በእምነት

የያቆብ ነገድ ሚካኤል
ለእስራኤል ሚካኤል
ጠባቅያቸው ነህ ሚካኤል
መልአከ ሀይል ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት(2)
ኣዝ

በስእል ፊት ሚካኤል
እሰግዳለሁ ሚካኤል
መጥተህ አነጋግረኝ ሚካኤል
አለሁ በለኝ ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት(2)
ኣዝ

ነጸብራቃዊ ሚካኤል
ተክኖ ልብስህ ሚካኤል
ሃመልማለ ወርቅ ሚካኤል
አይን ዘርግብ ሚካኤል
ፍቅርን አድለን ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኛ አባት(2)

Download it from here

ሉዑል እግዚአብሔር

ሉዑል እግዚአብሔር (2) ምስጋና ይገባዎል (2)
ለዚህ ሰዓት ለዚህ ዕለት በሰላም በጤና ላደረሰን(2)

Download it from here

ሰዎች ደስ ይበለን

ሰዎች ደስ ይበለን በአምላካችን
ከሃጥያት ባርነት ነጻ ላወጣን
ተነሱ ናመስግን ውለታው ብዙ ነው
ምን ይከፈለዋል ተመስገን ብቻ ነው

ከሃጥያት በሽታ ወድቄ ሳለሁ
መድሀኒት ክርስቶስ ከውድቀት ያነሳኝ
ስጦታው ብዙ ነው ለኔ የሰጠህኝ
ተመስገን ብቻ ነው አምላክ ላንተያለኝ
ኣዝ

እንደ በርጠሚዎስ እውር የነበርኩኝ
ዛሬ ግን ባአምላኬ ድህነት አገኘሁኝ
ሕጉ ለመንገዴ ብርሃን ሆኖኛል
የሱ ስለሆንኩኝ ሰላምን ተርፎኛል
ኣዝ

በድንቅ አጠራርህ በፍቅር ጠራህኝ
ካጋንንት ስራ ነፃ ያወጣህኝ
ኣልፋና ኦሜጋ ዘልአልም የምትኖር
ኤልሻዳይ የሆንከው አማኑኤል ተመስገን
ኣዝ

የእዳ ደብዳቤን ጌታ የቀደደው
የማዳንን ስራ በአይኔ አይቻለው
ቸርነቱ ኣያልቅም ድንቅ የሆነ ጌታ
ስሙን እናመስግን እንዘምር በእልልታ
ኣዝ

Download it from here

ትርሲተ ወልድ

ትርሲተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ሀደረ ለእሌሃ ሀሀደረ (2)
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሰናይትየ ማርያም ድንግል (2)

Download it from here

ኣዕረግዋ

ኣዕረግዋ መላእክት ውስተ ሰማያት (2)
ኣዕረግዋ መላእክት ውስተ ሰማያት (4)

Download it from here